እኛ ማን ነን (ስለማንነታችን)
1-ለ-1 ኢትዮጵያ በኪነቱ ባለሙያ በኦላፉር ኤልያንና በታሪክ አዋቂዋ ማሪያን ክሮ የንሰን ሕብረት በ1997 ዓም ተቋቋመ። የዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋናው ትኩረት ለጉዳት ተጋልጠው ያሉ ኢትዮጵያውያን ሕጻናትን ሕይወትና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ነው።
በሶስት አውሮፓ ከተሞች፤ ማለትም በርሊን፣ኮፐንሀገን እና ዙሪክ የተመዘገበ አነስተኛ በጎ አድራጊ ድርጅት፤ 1-ለ-1 ኢትዮጵያ ክሄክላ ድርጅት የሚያገኘውን የገንዘብ እርዳታ፤ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰሩ ለታቀዱ ምርጥ ውጥን እቅዶች ይለግሳል። የእቅዶች የሥራ ክንውኑንም ሃገሪቱ አዲስ አበባ ውስጥ ከአሉን ተባባሪዎች ጋር በመሆን የእለቱን ተግባር አዚያው ሆነው በሚከታተሉት ሰዎች ጥረት በሕብረት ያካሄዳል።
ከሃገሬው ሕዝብ ጋር በሕብረት መሥራታችንም የኢትዮጵያዊነት ስሜቱ ይበልጥ እንዲሰማ ከማድረጉም በላይ፣ተባባሪዎቻችን የራሳቸው እቅድ በመሆኑ የበለጠ ባለቤትነት እንዲሰማቸው ይረዳናል። እኛም እቅዶች ሁሉ በወግ ተቀላጥፈው እንዲካሄዱና ዘላቂነት እንዲኖራቸው፣ ይህን መሰል ትብብር የሚያሻ መሆኑን አምነን እንቀበላለን። ጥረታችንም ውጤታማና ዘላቂነት የሚኖረው መሆኑ እንዲረጋገጥ፣አሁንም ሆነ ወደፊት ለልጆቹ አስፈላጊውን ነገሮች እያስተዋልን፤ እንደአስፈላጊነቱ ጥረታችንን በሚገባ ለማስተካከል እንጥራለን።
ጥረታችንም የሚጠበቀውን ከፍተኛ ውጤት እንዲያስገኝና እቅዶችም አመርቂ እንዲሆኑ፤በየጊዜው የስራውን እንቀስቃሴ የሚያስተውሉልን የልማት እቅድና የሥራ ጥራት ባለሙያዎችን እያስመጣን ግንዛቤያቸውን እንቀበላለን። በዚህም ረገድ፣ሥራችን ሁሉ ከሃገሩ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና ወቅታዊ እንደሆነም ማስረጃ ይሆነናል።
ተግባራችን (ምንድን እንደምንሠራ)
1-ለ-1 ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለአደጋ የተጋለጡ ሕጻናትን ሕይወታቸውን ለማሻሻል ይጥራል። በዚህም ረገድ የሚያተኩረው፣ ወላጆች የሌላቸውን ማሳደጊያ ቤት ውስጥ ያሉትንና ወይንም በጊዚያዊ ተንከባካቢ የመቆያ ሥፍራ ውስጥ ያሉትን ሕጻናት በመርዳት ነው። ሕጻናት ከሥፍራ ሥፍራ በመንከራተታቸው የተነሳ ከባድ የመንፈስ ጭንቀትና መረበሽ ሰለሚደርስባቸው፣እድገታቸው እንዲስተካከል እንክብካቤ ያሻቸዋል። ከአንድ ሥፍራ ወደሌላ ሥፍራ መንከራተቱ ከእሩቅ ወደ ቅርብም ሆነ ከቅርብ ውደ እሩቅ ፣ በደፈናው የመኖሪያ ቦታ መለዋወጡ እድገታቸውን ያቃውሰዋል። ስለዚህም እኛ ልጆች ጤናማ ሕይወት እንዲኖራቸው ደስታ ያለበት የልጅነት አስተዳደግ ሁኔታ እንዲሆንላቸው፣አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር እንጥራለን። እቅዶቻችንም በሙሉ ይህን መሰል ለልጆች አመቺና አስደሳች የአስተዳደግ ሥፍራ በማዘጋጀት ላይ ያተኮሩ ናቸው። የምንሠራባቸውም የሥራ መስኮች የሚከተሉት ናቸው፤
የልጆችን ተንከባካቢዎች ማሰልጠን፣
በ 1-ለ-1 ኢትዮጵያ የሕጻናት ተንከባካቢ ሥልጠና ፕሮግራም መሠረት፣ኢትዮጵያውያን የሕጻናት ተንከባካቢዎችን በሞያው እያሰለጠንን፣ማደጊያ ቤት ያሉት ሕጻናት ሁሉ በሥርዓት ተጠብቀው እንዲያድጉ ድጋፍ እንሰጣለን። አሳዳጊዎችም እውቀት እየቀሰሙ፣ችሎታቸውን በማዳበር፣ለልጆች በመራራት፤የልጆቹን ስሜት እየተረዱ ለየሁኔታው በርህራሄ ተገቢ የሆነውን እርምጃ በመውሰድ ልጆችን ያሳድጋሉ። የሙያ ሥልጠናውም ለየተሳታፊው እንደችሎታው/ዋ የሚስተካከል ሥልጠና ይሆናል። ፕሮግራሙ ዘላቂነት እንዲኖረው፣ በሶስት ደረጃ ተከፋፍሏል።
ደረጃዎቹም ፣ትምህርቱን መማር፤የተማሩትን በየዕለቱ ተግባራዊ ማድረግ፤ያወቁትን ለሌሎች ማስተማር ናቸው። ይህ የሥልጠና ፕሮግራም የሕጻናት ማሳደጊያ ቤት አስተዳደርንም ያጠቃልላል።ይህ ሥልጠና በ 2002 ዓ ም የተጀመረ ቢሆንም፣ከየሁኔታው እና ከጊዜው ጋር ኣብሮ እንዲሄድ በየጊዜው እያሻሻልነው ስለሆነ ወቅታዊ ነው።ሕጻናት ማሳደጊያዎችን መደገፍ፤
ከ 1996 ዓም ጀምሮ ከመንግሥትም ሆነ ከግል ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየሰራን እንገኛለን፣ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ የሕጻናት ማሳደጊያዎች ጋር በመተባበር፣ጥንቃቄ የተሞላበት፣የማያሰጋ፣ ምቹ ሁኔታ የሰፈነበት፣የሚያዝናና የሕጻናት ማደጊያ ቤቶች እንዲኖሩም እየሞከርን ነው። ይህም በሽግግር ላይ ለሚገኙ ሕጻናት እንዲረጋጉ አስፈላጊ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ በሕጻናት ስነ-ልቦና እና በጤናቸው ላይ፣በዕለት ጥበቃቸው አያያዝና በማሳደጊያው ቤቶቹ ጽዳት ጉዳይ ላይ ሊደረግ በሚችለው የመሻሻል እደሳ ላይም አትኩረን በመስራት ላይ ነን። ሥራውም ኢትዮጵያ ካሉት የሕጻናት ማሳደጊያዎች ጋር በሚደረገው የማያቋርጥ የቅርብ ውይይት የሃሳብ እና የሥራ ልምድ ልውውጥ ላይ የተመሰረተ ነው። በአሁኑ ወቅትም እንደዚሁ የአንድ ተባባሪያችንን ማሳደጊያ ስፍራ በተገቢው ረገድ ከልማቱ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ መልክ አዋህደን አሻሽለን በማደስ ላይ እንገኛለን።የሃገሬው ሕብረተ-ሰብ ድጋፍ፤
በአዲስ አበባ ውስጥ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች 1-ለ-1 ኢትዮጵያ በአካባቢው ላሉ ልጆችና ወላጆች የድጋፍ ፕሮግራም በመስጠት ይረዳል። በዚህ ፕሮግራም አማካይነትም፣የልጆች ቤተሰቦች ለትምሕርት የሚሆን ቁሳቁስ እና፤ ለህክምና የሚሆን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙ ሲሆን፣ይህም የልጆቹን ትምህርት እና ደህንነታቸውን ለመከታተል ይረዳናል። የሕክምና እርዳታውና የገንዝብ ድጎማው ለአካባቢው ደካማ አረጋውያንም ይሰጣል። ይህን መሰል ፕሮግራም በመደገፍ፣ሕጻናትና ወላጆቻቸው በሚያውቁት አካባቢ እንዲቆዩ አድርገን፣ከመፈናቀል በማዳን፣ሕይወትን ሙሉ ከማይለቅ የመንፈስ መናወጥ ችግር እናድናቸዋለን ብለን እንገምታለን።የእውቀት ልውውጥ፣የሥራ ልምድ መገልገያዎች፣የሃገሬው ችሎታ፤
ከባለሞያዎችና ከሃገሬው ተባባሪዎቻችን ጋር ዘወትር ሃሳብ በመለዋዋጥ፣የሥራ ስልታችንን ለማሻሻል ሳንታክት ሰለምንጥር፣የሥራ ዘዴያችንም ሆነ የምንገለገልበት መሳሪያችን ሁሉ ለሁኔታው አጥጋቢ መሆኑን ከማረጋገጥ ቸል አንልም። ከዚህም በላይ፣ለተባባሪዎቻችን ሁሉ ካገኘነው የሙያ መሻሻል ጥበብ በማጋራት፣ የሙያው ልውውጥ እንዲቀጥልና አዳዲስ ቴክኖሎጂና ሥልጠናው እንዲደርሳቸው እናልማለን።ራዕይና እሴት
1-ለ-1 ኢትዮጵያ፣ ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ሕጻናትን የመርዳት ስብአዊ ሃላፊነት እንዳለብን ይሰማናል። ይህንንም ኃላፊነት ለመወጣት፤መጀመሪያ ሕጻናቱን ተቀዳሚ በማድረግ፣እያንዳንዱ ሕጻን ያለበትን ሁኔታ በደንብ ተረድተን፣የምንሰጠው አገልገሎት ማብቂያ ድረስ ለመደገፍ እንጥራለን። ሥርዓት ባለው ትክክለኛ አሰራር ሰለምናምንም፣በከፍተኛ እና ትክክለኛ ተግባር ሥራችንን እንቀጥላለን፣ እንደግፋለንም።
የ 1-ለ-1 ኢትዮጵያ ራዕይ፤
የ 1-ለ-1 ኢትዮጵያ እሴት
የ1-ለ-1 ኢትዮጵያ ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ሁሉ አስደሳች፣የማያሰጋ፣ጤናማ፣ልጅነት እንዲኖራቸው ይመኝላቸዋል። ይህም ራዕይ እውን እንዲሆን፣ኢትዮጵያውያን ግልጋሎት ሰጪዎች ተንከባካቢዎችን በማሰልጠን፤ሕጻናቱ ወደማደጊያ ስፍራ በሚሸጋገሩበት ወቅት ብዙ ሳይጨነቁ፣ተዝናንተው ቶሎ እንዲላመዱ አመቺ ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንሞክራለን።
- ዘወትር የሕጻናቱን አመለካከት መረዳት፤(ሁኔታዎችን እንደእነእርሱ ማየት)፤
- ከአገሬውና ከተባባሪ አካል ጋር እንደአካባቢው ሁኔታ አብሮ መሥራት፤
- ያለማቋረጥ፤እውቀትን፣ የሥራ መገልገያ ልምድን እና ሃሳብን፣መለዋወጥ፤
- ዘላቂ የሆነና ለረጂም ጊዜ የሚቆይ አርኪ ተግባር መፈጸም፤
- ለውጥ አምጪ የሆነ ሃሳብ ሁሉ፣ተግባራዊ እንዲሆን ማበረታታት።
የመገልገያ ሰንዱቅ፤ጠቃሚ ቅርሶች፤መገልገያዎች፤
የሃሳብና የሥራ እውቀት ስልት መለዋወጡ ከሥራ ልምድ መቀያየሩ ጋር ሥራችን እንዲሳካ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን መሰሉንም የሃሳብ ልውውጥ ለማቀላጠፍ እንዲረዳን፣የመንጠቀምባቸውን መገልገያ ስልቶች፤ለሌሎች መሰል ድርጅቶች ይጠቅም ይሆናል በማለት፣ከበታች እዚሁ ገጽ ላይ፣ ደረ-ገጽ መግቢያ ሀረጎችን አስፍረናል። ሆኖም ሁሉም የሚጠቅሙት፣ አንድን ሕጻን ከቦታ ቦታ ሲንከራተት ሊደርስበት ከሚችለው ጭንቀትና የማንነቱ መዘበራረቅ ማትረፍ ነው።
ሰነዶችን አውርደው (ዘርግፈው) ለማንበብ ከፈለጉ፣ይህን አደራሻ ተጠቅመው ምልክት ‘ከትበ-ገበር’ በመጫን ይላኩልንና ‘የይለፍ-ቃል’ እንሰጥዎታለን።
ከቦታ-ቦታ በመዘዋወር ላይ ላሉ ሕጻናቶች ሥነ-ምግባራዊ አያያዝ፤ – ይህ መመሪያ ሕጻናትን በተረጋጋ መልክ ጭንቀት አልባ በሆነ ሁኔታ ልጆች አስተዳደጋቸው ሳይናጋ፣ የወደፊት ሕይወታቸው ሳይቃወስ፣ ሊሸጋገሩ የሚችሉበትን ተግባራዊ ዘዴዎች ይገልጻል።
ከቦታ-ቦታ በመዘዋወር ላይ ያሉ ሕጻናቶችን ሥነ-ምጋባራዊ አያያዝ (ሰነድ) (ይህ ሰነድ የተለየ ስም ሊሰጠው ይችል ይሆናል)።
1-ለ-1 ኢትዮጵያ ሕገ-መሠረት፤ ድረ-ገጽ አደራሻ፤ አዲስ አበባ (ማግኛ ሃረግ) - 1-ለ-1 ኢትዮጵያ ሕገ-መሠረት፣ለሌሎች መሰል በጎ አድራጊ ድርጅቶች በመሰረቱ፣ ምሳሌ ለመሆን እና የሥነ-ምግባር ማመንጫ ፣ የሥርዓትና የእሴት ደረጃ ሊሆን ይችላል ብለን እናምናለን።
የአንድ ሕጻን የግል ማህደር (ማግኛ ሃረግ) - የሕጻን የግል ማህደር፣ የአንድን ልጅ እድገት ዝርዝር የያዘ መገልገያ
የሕጻን መዝገብ፣ የአንድን ሕጻን ዕድገት ማስረጃ ለመመዝገብ ያገለግላል (ማግኛ ሃረግ)
የሕጻን መሰረታዊ አስተዳደግ መቃኛ (ማግኛ ሃረግ) - የአንድን ከስፍራ-ወደስፍራ ዝውውር ላይ ያለ ሕጻን መሰረታዊ አስተዳደግ፣የአካል፣የስነ-ልቦና፣የቤተ-ሰብም ሆነ ሌላ የዘመድ እና የወዳጅ ሁኔታ ለመቃኘት ይረዳል። ይህም ዘዴ፤ የልጁን/ልጂትዋን ሕይወት ታሪክ ይመዘግባል።
እርዳታ ለመስጠት ከፈለጉ፤
1-ለ-1 ኢትዮጵያ ተግባሩን የሚመራው 1-ለ-1 በሚል መሠረታዊ አላማ ነው። ይህም አንድ ብር በእርዳታ ሲገኝ፣ያው አንድ ብር በሙሉ እንደአለ እዚያው እቅዱ ላይ ይውላል። ከተዋጣው ገንዘብ ላይ፣ ምንም ዓይነት የአስተዳደር ወጪ አይነሳለትም። ዋናው አላማችንም የምንሠራውን ሥራ ሁሉ አንድ በአንድ እያስተዋልን፣ እርምጃችንን በጥንቃቄ ተከታተልን፣ለፍጻሜ ማብቃት ነው። ይህም መዋጮው ሁሉ ምንም ሳይባክን፤በተቻለ መጠን ተግባር ላይ እንዲውል ለማረጋገጥ ይበጃል።
ጥሬ ገንዝብ ለመስጠት 1-ለ-1 ኢትዮጵያ በሄክላ ድርጅት ጥላ ስር ሰለሚሰራ፤በሚያመችዎ ባንክ በኩል ለሄከላ ድርጅት ጀርመን ወይም ስዊዘርላንድ ሊለግሱ ይችለሉ።
1-ለ-1 ኢትዮጵያን ለመርዳት ለሚሹ የአሜሪካን ሃገር ነዋሪዎች፤ድረ-ገጽ አድራሻችንን ጎብኝተው info(a)121ethiopia.org እርዳታቸውን ለመለገስ ይችላሉ።
Germany:
Account name: Hekla Foundation gGmbH Bank: GLS Bank
Branch: Berlin
Bank number: 43060967
Swiftcode: GENODEM1GLS
Account number: 1126396500
IBAN: DE29 4306 0967 1126 3965 00
Switzerland:
To make a donation in Swiss Francs, please use this number:
Account name: Hekla Stiftung
Bank: UBS
Branch: Zurich
Swiftcode: UBSWCHZH80A
Account number: 230-368792.40N
IBAN: CH25 0023 0230 3687 9240 N
To make a donation in Euros, please use this number:
Account name: Hekla Stiftung Bank: UBS
Branch: Zurich
Swiftcode: UBSWCHZH80A
Account number: 230-368792.61K
IBAN: CH54 0023 0230 3687 9261 K
To make a donation in US Dollars, please use this number:
Account name: Hekla Stiftung
Bank: UBS
Branch: Zurich
Swiftcode: UBSWCHZH80A
Account number: 230-368792.60P
IBAN: CH97 0023 0230 3687 9260 Pአድራሻችን
Strandagervej 28
DK-2900
Hellerup Denmark
+ 45 39 46 01 50
info(a)121ethiopia.org